አማርኛ (Amharic)

2020

ፌብሯሪ 25/2020 QuickNotes


የትምህርት ቦርድ የ2021ን የሥራ ማስኬጃ በጀት አጽድቋል

የትምህርት ቦርድ ለ2021(FY) የበጀት ዓመት ለጊዜዉ የ $2.805 ቢሊዮን ዶላር የሥራ ማስኬጃ በጀት ለማጽደቅ በአንድ ድምፅ ወስኗል/ተስማምቷል። ይህም ከ2020 የበጀት ዓመት $124.1 ጭማሪን ያካትታል። ይህ በጀት MCPSን ትርጉም ያዘለ የምዝገባ እድገት እንዲያስተዳድር እና በተማሪ ስኬት ላይ ልዩነቶችን ለማስወገድ በስልታዊ ኢንቨስትመንቶች/የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት ላይ ትኩረት እንዲሰጥ ያደርገዋል።

ኣብዛኛው የ$124.1 ሚልዮን የወጪ ጭማሪ የሚውለው ቁጥራቸው በማደግ ላይ ለሚገኘው ተማሪዎች አገልግሎቶችን ለማቅረብ፤ ቀጣይ ደሞዞችንና ጥቅማጥቅሞችን ለመሸፈን፤ እና ተጨማሪ የግብረቶች ወጪዎችን ለማስተዳደር/ማኔጅ ለማድረግ ነው።

ስትራቴጂያዊ የሆኑ ቁልፍ የሥራ ክፍሎችን ለማስፋፋት እና ለመተግበር በቀረበው የበጀት እቅድ ላይ $23.7 ሚሊዮን ዶላር ተካቷል። ይህ የሚያካትተው፦

 • ለተጨማሪ የእንግሊዘኛ ለሌሎች ቋንቋዎች ተናጋሪዎች መምህራን እና ካዉንስለሮች/አማካሪዎች፤
 • የቅድመ ሙዓለህፃናት መቀመጫዎችን/ክፍሎች ማስፋፋት፤
 • የቋንቋ ትምህርት እድሎችን ማስፋት፤
 • ለጠንካራ የኮርስ ሥራ ይበልጥ ተደራሽነት እንዲኖር ለማድረግ ሦስት አዲስ ሪጅናል ኢንተርናሽናል ባከሎሬት ማእከሎችን/regional International Baccalaureate centers መፍጠር።
 • የተማሪን የአእምሮ ጤንነት እና ደህንነትን ለመደገፍ የአእምሮ ጤንነት ድጋፍ ሠራተኞችን መጨመር፤
 • በአዲሱ የሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት/Seneca Valley High School የአፕካውንቲ የሥራ-ሙያ ዝግጁነት ማእከል/ሀብ መክፈት፤
 • ለቋንቋ እና ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ፣ እና ሒሳብ ፕሮግራሚንግ ተጨማሪ ድጋፍ መስጠት፤
 • ፍትሃዊነት እና የፈጠራ ተነሳሽነት/ማበረታቻ፤ እና
 • ሁሉም የመማሪያ ክፍሎች የተለያየ ዳራ ባላቸዉ ከፍተኛ ብቃት ያላቸው አስተማሪዎች እንዲኖራቸው ለማድረግ የመምህራን ምልመላ እና ማቆየት ጥረቶችን ማስፋፋትና ማጎልበት።

ቦርዱ የበጀት ጥያቄውን ለMontgomery County Executive Marc Elrich and the County Council (የካውንቲ ስራ አስፈፃሚ ለማርክ ኤልርች እና ለካውንቲ ምክር ቤት) ማርች 1/2020 ያቀርባል። የካውንቲው ስራ አስፈፃሚ Elrich/ኤልርች የስራ ማስኬጃ በጀት ረኮመንዴሽኑን ማርች 16 እንደሚያሳውቁ ይጠበቃል። የሞንተጎመሪ ካዉንቲ ምክር ቤት የካውንቲ በጀቱን ኣስመልክቶ የመጨረሻዉን የበጀት ዉሳኔ በሜይ 21/2020 ከማሳለፉ ኣስቀድሞ በኤፕረል ወር ህዝባዊ ችሎት ያካሂዳል። ከካውንቲው ምክር ቤት እርምጃ በኋላ ፣ የትምህርት ቦርዱ የመጨረሻውን የ FY/በአ 2021 የሥራ ማስኬጃ ባጀት ለማፅደቅ ጁን 11/2020 ድምጽ ይሰጣል።

በ ESOL ፕሮግራም ላይ የተደረጉ ለውጦችን ለማብራራት ስብሰባዎች ይካሄዳሉ

እንግሊዝኛ ለሌሎች ቋንቋዎች ተናጋሪዎች (ESOL) ፕሮግራምን አስመልክቶ በቀጣይ ስለሚደረጉ ለውጦች ለመማር/ለማወቅ ሰራተኞች፣ወላጆች እና የማህበረሰብ አባላት ለተከታታይ ስብሰባዎች ተጋብዘዋል። እነዚህ ለውጦች በመካከለኛ እና በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ ESOL ፕሮግራሞች ተማሪዎች ላይ ያነጣጠሩ ሲሆን በበርካታ ምክንያቶች የተደረጉ ናቸው ፦

 • የ ESOL ተማሪዎች ለክፍል-ደረጃ የይዘት ትምህርቶች ተደራሽነት እንዲኖራቸው ለማረጋገጥ
 • የ ESOL ተማሪዎችን የምረቃ መጠን መጨመር/ማሳደግ
 • እነዚህ ተማሪዎች ለኮሌጅ እና ለስራ ዝግጁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ፣ እና
 • ለሁሉም የ ESOL ተማሪዎች ከፍተኛ ጥራት ያለው የእንግሊዝኛ ቋንቋ እድገትን ለመጠበቅ

ስብሰባዎቹ የሚካሄዱት ከ6–7:30 p.m. በ ፦

ሮብ፣ ፌብ. 26

Rocking Horse Road Center

All Purpose Room

4910 Macon Road, Rockville

ሐሙስ፣ ፌብ. 27

Watkins Mill High School /ዋትኪንስ ሚል ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት

ሚዲያ ማእከል/Media Center

10301 Apple Ridge Road, Gaithersburg

ሮብ፣ ማርች 18

East Montgomery Regional Service Center

3300 Briggs Chaney Road, Silver Spring

የዳሰሳ ጥናት ለልዩ ትምህርት ወላጆች ክፍት ነው

ልዩ ትምህርት እና የተያያዙ ኣገልግሎቶችን ( እንደ የንግግር፣ አካላዊ እና የሥራ/ሙያ ቴራፒ፣ ወዘተ ያሉ)የሚያገኙ ልጆች ወላጆች ወይም ኣሳዳጊዎች የዚህን አመት የሜሪላንድ የልዩ ትምህርት ወላጅ ተሳትፎ ዳሰሳ ጥናት/Maryland Special Education Parent Involvement Survey እንዲሞሉ ይጠየቃሉ።

የምትሰጡት መረጃ በህዝብ ት/ቤቶች የሚቀርቡ ልዩ ትምህርትና የተያያዙ ኣገልግሎቶችን ለማሻሻል ስቴቱ የሚያደርገውን ጥረት ለመምራት ያግዘዋል። አገልግሎቶችን ለሚቀበሉ ለእያንዳንዱ ልጅ አንድ የዳሰሳ ጥናት ይሙሉ። የዳሰሳ ጥናቱ ሚስጢራዊ ነዉ እናም በመስመር ላይ/ online መሙላት ይቻላል

የዳሰሳ ጥናቱ መፈጸሚያ የጊዜ ገደብ አርብ፣ ሜይ 15 ነው።

የሜሪላንድ የቅድመ ትምህርት ቤት ልዩ ትምህርት የወላጅ ተሳትፎ ዳሰሳ ጥናት/ቅኝት

የሜሪላንድ የልዩ ትምህርት የወላጅ ተሳትፎ ዳሰሳ ጥናት/ቅኝት

የስፕሪንግ የቲያትር መርሃግብር ወጣ ፤ ድራማዎን ያግኙ!

በመላ የት/ቤት ስርአት፣ በመካከለኛ ደረጃ እና በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በሁለቱም፣ ለስፕሪንግ የትያትር ዉጤቶች/ፕሮዳክሽን መጋራጃው በመነሳት ላይ ነው። ከማርች መባቻ አካባቢ ጀምሮ እስከ ሜይ የሚካሄዱትን እነዚህን ታላላቅ ትያትር ስራዎች ለማየት ከአሁኑ ቲኬትዎን ይግዙ። From “Mamma Mia!” and “Frozen” to “The Great Gatsby” and “Chitty Chitty Bang Bang Jr.” መድረክ ላይ ለሁሉም ሰው የሚሆን አንድ ነገር አለ።

2019–2020 የስፕሪንግ ቲያትር መርሃግብር

ቅድመ-ሙአለህፃናት/ሄድ ስታርት ምዝገባ (Head Start Registration) ማርች 2 ይጀምራል

ለ2020-2021 የትምህርት አመት ልጃቸውን ለMCPS ቅድመ-ሙአለህፃናት ወይም ሄድ ስታርት ክፍል ማስመዝገብ የሚፈልጉ ከሰኞ፣ ማርች 2 ጀምረው ማስመዝገብ ይችላሉ። የልጆች እድሜ ሴፕተምበር 1/2020 ወይም ቀደም ብሎ  4 አመት መሙላት አለበት፣ ወላጆችም የገቢ መስፈርት ማሟላት ይኖርባቸዋል።

ስለብቃት መመርያዎች፣ የማህበረሰብ ምዝገባዎች ቦታ እና ጊዜ ወይም ማመልከቻውን ለመሙላት ስለ ተፈላጊ ሰነዶች ተጨማሪ መረጃዎች፣ 240-740-4530 ይደውሉ ወይም MCPSን ድርጣብያ ይጎብኙ።

የቅድመ-ሙኣለህፃናት/ሄድ ስታርት ምዝገባ ፕሮግራም

ለሀገር አቀፍ የህዝብ ጤና ሳምንት የካውንቲ አቀፍ የጤና በዓል ታቅዷል፤ ድርጅቶች ለዝግጅቶች እንዲመዘገቡ ይበረታታሉ

የሞንጎመሪ ካውንቲ የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎቶች መምሪያ ከጤናማ ሞንትጎመሪ ጋር በመተባበር፣ ብሔራዊ የህዝብ ጤና ሳምንትን (ከኤፕሪል 6-12) ለማክበር ሁለተኛውን የካውንቲ አቀፍ የጤና በዓል/ትርኢት በማቀድ ላይ ነዉ። እንደተለመደዉ በአንድ አካባቢ የጤና ትርኢት ከማድረግ ይልቅ፣የአጎራባች ማህበራት ፣ የጤና ድርጅቶች ፣ ትምህርት ቤቶች ፣ የንግድ ድርጅቶች እና ሌሎች የመንግስት ኤጀንሲዎች ከጤና ጋር የተዛመዱ ዝግጅቶችን በጠቅላላ ካዉንቲዉ ዉስጥ እንዲያስተናግዱ አዘጋጆች እየጠየቁ ነው። ከጤና ሲምፖዚየሞች እና ምርመራዎች እስከ የጤና ማሳያ ድረስ፣ በጣም ትልቅ ወይም ትንሽ ነዉ የሚባል ምንም ክዉነት/ዝግጅት የለም።  በሞንጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ማንኛውም ቡድን መሳተፍ ይችላል። አንድ ዝግጅት በኤፕሪል 6-12 ሳምንት ባለው ጊዜ ውስጥ የታቀደ ከሆነ፣ እንደ ብሔራዊ የህዝብ ጤና ሳምንት ዝግጀት ተደርጎ እንዲቆጠር እባክዎን ያስመዝግቡ።  ግቡ “የዓለም ትልቁ የጤና ትርኢት” ማስተናገድ ነው።

ዝግጅቶችን ያስመዝግቡ በNPHW Register Your Event።  በኤፕሪል 1 የሚመዘገቡ ቡድኖች በካውንቲው ምክር ቤት በ NPHW ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ከሚያረጋግጥ እወጃ/መግለጫ ጋር እዉቅናን ያገኛሉ። እወጃዉ/መግለጫዉ ለኤፕሪል 21 ቀን ተይዞለታል።

በተጨማሪም በ NPHW ወቅት የታቀደው፣ ሁለተኛው አመታዊ  Ulder J. Tillman Memorial Lecture/ የመታሰቢያ ንግግር ሲሆን፣ ይህም የካውንቲዉ የቀድሞ የጤና መኮንን እና የህዝብ ጤና አገልግሎት ኃላፊ የነበሩት Dr. Tillman ከ 2004 እስከ ሞቱበት 2017 ድረስ ላበረከቱት አስተዋፅኦ እዉቅና የሚሰጥበት ክዉነት ነዉ።  የዚህ አመት ንግግር ስነልቦናን የሚያዛባ/ለከፋ የስሜት መጎዳት ስለሚዳርግ እንክብካቤ እና በተጋላጭ ማህበረሰቦች ላይ የሚያተኩር ሲሆን፣ ለሰኞ ኤፕሪል 6 እኩለ ቀን ላይ በሲልቨር ስፕሪንግ ሊደረግ መርሀግብር ተይዟል።  ዝግጅቱ ለማህበረሰብ በነፃ ክፍት ይሆናል፣ ነገር ግን አስቀድሞ መመዝገብ አስፈላጊ ነው። ምሳ ይቀርባል። ተጨማሪ መረጃ እና ምዝገባ በUlder J. Tillman Lecture in Public Health

ስለ ብሄራዊ የህዝብ ጤና ሳምንት ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ፣www.nphw.org ይጎብኙ።  ስለ ሞንትጎመሪ ካውንቲ ዝግጅቶች፣ እና ለመጀመር መሣሪያዎች እና ሀሳቦች መረጃ፣ ይጎብኙ www.healthymontgomery.org ወይም በኢሜይል Brittany Foushee ን በ britanny.foushee@montgomerycountymd.gov ወይም 240-777-1704 ያግኙ።